አዲስ አበባ ፣ መስከረም 5 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሶስት ዓመታት በፊት የተተከሉት የቡና ዛፎች የአረንጓዴ ዐሻራን ፍሬ እያፈሩ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ሥነ-ምህዳሩን ከማረጋጋት ባለፈ የግብርና ደን ልማትን በማጎልበት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
ለአብነትም ከሶስት ዓመታት በፊት የተተከሉት የቡና ዛፎች የአረንጓዴ ዐሻራን ፍሬ እያፈሩ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡