አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮችን እንዲመረጡ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የተወካዮች ልየታ ስራ በመዲናዋ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እየተደረገ መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በጠዋቱ መርሃ-ግብር ላይ ለተሳታፊዎች ስለምክክር ፅንሰ ሀሳብ፣ ምክክር ለኢትዮጵያ ስላለው ፋይዳ፣ ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት፣ ስለተሳታፊ ልየታና አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት በኮሚሽኑ ባለሙያዎች ገለፃ ተደርጓል፡፡
በሁሉም ክፍለ ከተሞች ውስጥ እየተደረገ በሚገኘው የተወካዮች መረጣ በየክፍለ ከተማው ከሚገኙ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እያንዳንዳቸው 10 ሰዎችን አስወክለው በሂደቱ ላይ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።