የሀገር ውስጥ ዜና

በጅቡቲ በእሳት አደጋ ምክንያት ንብረታቸው ከተቃጠለባቸውን ዜጎች ጋር ውይይት ተደረገ

By Feven Bishaw

September 17, 2023

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በጅቡቲ ፒካዱዝ (PK12) ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በእሳት አደጋ ምክንያት ንብረታቸው ከተቃጠለባቸው ዜጎች ጋር ተወያዩ።

አምባሳደር ብርሃኑ በእሳት አደጋ ምክንያት ንብረታቸው ከተቃጠለባቸው ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትየጵያውያን ጋር መልሶ በማቋቋም ዙሪያ ነው በዛሬው ዕለት የመከሩት፡፡

በውይይታቸውም በአደጋው የተጎዱ ዜጎችን በማበርታት በአጭር ጊዜ ውስጥ መልሶ ለማቋቋም ኤምባሲው ያለበት አብይ ኮሚቴ እና የተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎች በማዋቀር በአስቸኳይ ወደስራ እንዲገባ መደረጉን ከጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡