የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን በ78ኛው የተመድ የመሪዎች ጉባዔ እየተሳተፉ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

September 18, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በኒውዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው 78ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ የመሪዎች ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡

  ጉባዔው በዘላቂ የልማት ግቦች ላይ እየመከረ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

  የኮቪድ-19 ተፅዕኖ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የጂኦፖለቲካዊ ግጭቶች ሀገራቱ የቀረጿቸውን ዘላቂ የልማት ግቦች ሀገራት ባቀዱት የጊዜ ሠሌዳ መሠረት እንዳይተገብሩ ማስተጓጎላቸው ተገልጿል፡፡

  የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ “ማንም የማይገለልባት የበለጸገች እና ሠላማዊ ዓለምን ዕውን ለማድረግ ጊዜው አሁን ነው” ብለዋል፡፡

  “የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ለማሳካትም ጊዜ ያለፈባቸውን የፋይናንስ ተቋማትና ማዕቀፎች መለወጥ እንደሚገባም” ነው ዋና ጸሐፊው ያሳሰቡት፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!