አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፀጥታ ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ሳይወስዱ የቆዩ ከ11 ሺህ 581 ተማሪዎች የሀገር አቀፍ ፈተናቸውን ለመውሰድ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ገብተዋል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲም ተማሪዎቹን ለማስፈተን ዝግጅት ማደረጉን አስታውቋል፡፡
ተፈታኝ ተማሪዎች÷ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ፈተናቸውን ማጠናቀቅ አለመቻላቸውን በማስታወስ በአሁኑ ወቅት ፈተናውን ለመውሰድ ሙሉ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ ያቋረጧቸውን የኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂና ሲቪክስ የትምህርት አይነቶችን ብሄራዊ ፈተና ይወስዳሉ መባሉን አሚኮ ዘግቧል፡፡