አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ለአምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 9ኛው አፍሪካ አቀፍ የወባ ትንኝ ቁጥጥር ማኅበር ዓመታዊ ጉባዔ እና ዐውደ – ርዕይ ተጠናቀቀ፡፡
ጉባዔው “በበሽታ ተኅዋስያን ላይ ከሚታዩ ሥጋቶች አንፃር ክትትልን እና ቁጥጥርን ማስተካከል” በሚል መሪ ሐሳብ ነው የተካሄደው፡፡
ማኅበሩ የኢትዮጵያ ቻፕተር ሊቀመንበር ድልነሳው የኋላው (ፕ/ር)÷ ጉባዔው በትንኝ የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመቆጣጠር እና ለማስወገድ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም ጉባዔው ክትትልን እና ቁጥጥርን ለማጠናከር ዓልሞ ተካሂዷል ማለታቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
የዘንድሮውን ጉባዔ ኢትዮጵያ በተሳካ ሁኔታ ማስተናገዷን የገለጹት ሊቀ- መንበሩ ÷ የቀጣዩን ዓመት ጉባዔ እንድታስተናግድ አይቮሪኮስት መመረጧን አስታውቀዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!