የሀገር ውስጥ ዜና

በባህርዳር ከተማ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የሰላም ውይይት እየተካሄደ ነው

By Feven Bishaw

September 22, 2023

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር “ሁለንተናዊና ዘላቂ ሰላም ለመገንባት የሁሉንም አካል ርብርብ ይጠይቃል” በሚል መሪ ሃሳብ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የሰላምና የልማት ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይት መድረኩ የባህር ዳርና አካባቢው ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሜጀር ጄኔራል ሙሉአለም አድማሱ፣ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።

የከተማ አስተዳደሩ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ጊዜው ታከለ ባቀረቡት ጽሑፍ በነበረው የጸጥታ ችግር ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።

ችግሮቹ በሰላማዊ መንገድ በዘላቂነት የሚፈቱ ናቸው ያሉት ጽሑፍ አቅራቢው መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ችግሮች እንዲፈቱ ከህዝቡ ጋር እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

የውይይቱ ዓላማ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ የህዝቡን ተሳትፎ ለማጠናከር መሆኑን ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በቀረበው ጽሑፍ ላይ ውይይት እየተካሄደ ሲሆን÷ በማጠቃለያው በሚመለከታቸው አካላት ቀጣይ አቅጣጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።