የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ትብብራቸውን ለማሳደግ ተስማሙ

By Feven Bishaw

September 23, 2023

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ ከ78ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን የተካሄደ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

በውይይታቸው የጋራ በሆኑ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ዘርፈ-ብዙ ትብብር ለማሳዳግም ተስማምተዋል።

ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን በያዝነው የፈረንጆቹ አመት መጨረሻ በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች በሚካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያን ሚና በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡