የሀገር ውስጥ ዜና

ወታደራዊ ሥልጠናዎችን ሲከታተሉ የቆዩ የክብር ዘብ ሠልፈኞች ተመረቁ

By Mikias Ayele

September 24, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለወራት በአየር ሃይል ኤር ፖሊስ ክፍለ ጦር ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የመከላከያ ክብር ዘብ ሠልፈኞች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ሌሎች የሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የአባላቱ መመረቅ ይስተዋል የነበረውን ደረጃውን የጠበቀ የሠው ሃይል እጥረት ለመቅረፍ እንደሚያስችል የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

በአየር ሃይል የኤር ፖሊስ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ወንዱ ወልዴ÷ ሠልጣኞች የሚገባቸውን እና የተሠጣቸውን ሥልጠና በወታደራዊ ዲሲፕሊን ታግዘው በሞራል መከታተላቸውን ተናግረዋል፡፡

ሰልጣኞች ሕግ እና ሥርዓትን፣ አሠራርና ዲሲፕሊንን እንዲሁም ወታደራዊ ባሕልና ጨዋነትን በሚገባ ተገንዝበው እንዲወጡ የሚያሥችል ሥራ መሠራቱንም አንስተዋል፡፡