የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ተገኝተው ማዕድ አጋሩ

By Feven Bishaw

September 28, 2023

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ20ኛው የአዲስ አበባ መስተዳድር የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ተገኝተው ለዐቅመ ደካሞች ማዕድ ማጋራታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገልጿል።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ የሚገኘው 20ኛው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።