የሀገር ውስጥ ዜና

የቦሮ ሽናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ጋሪ-ዎሮ” በዓል እየተከበረ ነው

By Feven Bishaw

September 28, 2023

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቦሮ ሽናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ጋሪ-ዎሮ” በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው፡፡

የ”ጋሪ-ዎሮ” በዓል በአሶሳ ከተማ በብሔረሰቡ አባቶች ምርቃት፣ በሲምፖዚየም፣ በባህላዊ ጭፈራና በተለያዩ ባህላዊ ሁነቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው።

“ጋሪ-ዎሮ ለይቅርታ፣ ለአብሮነትና ለሠላም” በሚል መሪ-ቃል በዓሉን የተመለከተ የፓናል ውይይት እየተካሄደ እንደሚገኝ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ተመስገን ዲሳሳ (ዶ/ር)፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።