የሀገር ውስጥ ዜና

አየር መንገዱ ወደ ቡጁምቡራ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ 11 አሳደገ

By Feven Bishaw

September 28, 2023

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የብሩንዲ ትልቋ እና የኢኮኖሚ ማዕከል ወደሆነችው ቡጁምቡራ ከተማ የሚያደርገውን ሳምንታዊ መደበኛ በረራ ወደ 11 ማሳደጉን አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ ከዚህ ቀደም በሚያደርገው ሳምንታዊ መደበኛ በረራ ላይ ተጨማሪ 4 ሳምንታዊ በረራዎችን በማከል ነው ከጥቅምት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ከተማዋ የሚደረገውን የመንገደኞች በረራ ቁጥር 11 ያደረሰው፡፡

እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ዋና ከተማ ባንጉይ ሶስት ሳምንታዊ የመንገደኞች በረራ አገልግሎት እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

በረራው ህዳር 15 ቀን 2023 ዓ.ም እንደሚጀምር ነው የአየር መንገዱ መረጃ ያመለከተው።