ስፓርት

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ ይጀመራል

By ዮሐንስ ደርበው

September 30, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጀመራል፡፡

ፕሪሚየር ሊጉ አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 9፡00 ላይ በሚያደርጉት ጨዋታ ነው የሚጀመረው፡፡

የነገው የጨዋታ መርሐ- ግብር ሲቀጥል 12፡00 ላይ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡