ስፓርት

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በ5 ኪሎ ሜትር የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ድል ቀናቸው

By Amele Demsew

October 01, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶች 5 ኪሎ ሜትር የሪጋ የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ድል ቀንቷቸዋል፡፡

አትሌት ሀጐስ ገ/ሕይወ ርቀቱን 12 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ቀዳሚ መሆን ችሏል፡፡

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ደግሞ ርቀቱን በ13 ደቂቃ ከ02 ሰከንድ በማጠናቀቅ 2ኛ ደረጃን ይዟል፡፡

በተመሰሳሳይ ÷አትሌት እጅጋየሁ ታዬ በሴቶች የ5 ኪሎ ሜትር የሪጋ የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች፡፡

አትሌት እጅጋየሁ ርቀቱን 14 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ሶስተኛ ደረጃን የያዘችው፡፡