አዲስ አበባ ፣ መስከረም 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሀዋሳ ከተማ ልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ዙሪያ ከከተማው ህብረተሰብ ክፍሎች ጋር እየተወያዩ ነው፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በውይይቱ ወቅት÷ የክልሉ መንግስት የከተማው ህብረተሰብ ጥያቄዎችን ለመፍታት በቅርበት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
የከተማው ህብረተሰብ ክፍል ቀድሞ በነበረው የከተማው አስተዳደር ላይ የክልሉ መንግስት የወሰደው የሪፎርም ስራ የሚበረታታ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን÷ የነበረው የመልካም አስተዳደርና የልማት ስራዎች ክፍተት ሊታረም እንደሚገባ አሳስበዋል ነው የተባለው።
ርዕሰ መስተዳድሩ የከተማው ህብረተሰብ ክፍልን ሃሳብ ለመስማት ውይይቱን ማመቻቸቱን መናገራቸውን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡