የሀገር ውስጥ ዜና

በፕላን የሚመሩ ከተሞችን መፍጠር ኅገ-ወጥነትን ለማስወገድ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተገለጸ

By Alemayehu Geremew

October 04, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፕላን የሚመሩ ከተሞችን መፍጠር ኅገ-ወጥነትን ለማስወገድ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ተናገሩ ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ “ስማርት ሲቲ”ዎችን ለመፍጠር በትኩረት መሥራት እንደሚገባ የገለጹት አቶ አብርሃም፤ ከተሞች በፕላን እንዲመሩ ማድረግ ከተሞችን በሥርዓት ለመምራት እንደሚያስችልም አስገንዝበዋል።

ከተሞችን ፅዱና ምቹ በማድረጉ ረገድ እያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት ሊሰማውና አካባቢውን ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል ።

ከተሞች በራሳቸው ገቢ እንዲተዳደሩ ማድረግ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ከተሞችን በካዳስተር ሥርዓት ማስገባት ሌብነትን ከመከላከል ባሻገር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

የ2016 በጀት ዓመት የሴክተር ጉባዔና የንቅናቄ መድረክ በሐዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በብርሃኑ በጋሻውና በተመሥገን ቡልቡሎ