አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር እና የመንግሥታቱ ድርጅት የሥነ-ሕዝብ ፈንድ (ዩኤንኤፍፒኤ) በሰብዓዊ ምላሽ እና ሌሎች ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማሳደግ ተስማምተዋል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ከመንግሥታቱ ድርጅት የሥነ-ሕዝብ ፈንድ ሰብዓዊ ምላሽ ዳይሬክተር ሾኮ አራካኪ እና የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተወካይ ኮፊ ኩዋሜ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ ጤና ሚኒስቴርና ዩኤንኤፍፒ በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ምክክር መደረጉን ሚኒስትር ዴኤታው በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ተቋማቱ በአደጋ እና ሰብዓዊ ምላሽ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ እንዲያሳድጉ ስምምነት ላይ መደረሱንም ጠቁመዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!