የሀገር ውስጥ ዜና

በሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ኦማር በሽር ማኒስ የተመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ

By Feven Bishaw

May 15, 2020

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ኦማር በሽር ማኒስ የተመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውም ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት ለልኡካን ቡድኑ አቀባበል አድርገዋል።