የሀገር ውስጥ ዜና

መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ምልምል ወታደሮች ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ

By Melaku Gedif

October 05, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአየር ሃይል አካዳሚ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ምልምል ወታደሮች ምረቃ ሥነ -ሥርዓት ተካሂዷል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ አየር ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የአየር ኃይል አባላት ተገኝተዋል፡፡

ምልምል ወታደሮቹ በኢፌዴሪ አየር ሃይል አካዳሚ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት ላለፉት ስድስት ወራት ስልጠናቸውን ሲከታተሉ እንደነበር የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

በዕለቱ በአካዳሚው በትምህርታቸው ውጤታማ ለሆኑ ተማሪዎች የማበረታቻና የእውቅና ፕሮግራም መካሄዱም ተገልጿል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!