የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች የውይይት መድረክ አካሄዱ

By Shambel Mihret

October 05, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች “አዲስ እሳቤ በአዲስ ክልል ወደ አዲስ ምዕራፍ ” በሚል መሪ ሃሳብ በወላይታ ሶዶ የውይይት መድረክ አካሂደዋል፡፡

በውይይቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ÷ አዲስ ዕሳቤን በመሰነቅ የክልሉ አመራሮች በመልካም አስተዳደር፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በሌሎች ጉዳዮች ለሕዝብ ምላሽ ለመስጠት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት የሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ከ120 ቀናት እቅዶች ውስጥ በ1 ወር ዕቅድ የተመዘገቡ ውጤቶችና መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮች ላይም ውይይት እንደተደረገ የወላይታ ዞን ኮሙኒኬሽ መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!