የሀገር ውስጥ ዜና

የሙስና መከላከል ስራን ለማጠናከር ከአይ ኤም ኤፍ ጋር በትብብር ለመስራት ውይይት ተካሄደ

By Melaku Gedif

October 05, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) ከዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ክትትል ልዑካን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷በኢትዮጵያ እየተከናወነ በሚገኘው የፀረ-ሙስና ትግል ዙሪያ በትኩረት መክረዋል፡፡

በቀጣይም የፀረ-ሙስና ትግሉን ለማጠናከር በትብብር በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡