አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የአፍሪካ ህብረትና ተመድ በሰላምና ፀጥታ ዘርፍ የተቀናጀ ጥረት እና ትብብር እንዲያደርጉ ጠየቁ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ዛሬ በአዲስ አበባ ሲያደርጉት የነበረውን የስራ ጉብኝት አጠናቀዋል፡፡
አቶ ደመቀ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግርም፥ መንግስት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በተሟላ መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን ቁርጠኛ መሆኑንና ለቀጣናው መረጋጋትም ገንቢ ሚና እንደሚጫወት አንስተዋል።
የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰርጂዮ ፍራንካ ዳኒዝ በበኩላቸው ፥ የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት በሁለቱ ዓለም አቀፍ አካላት መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ወሳኝ ሚና እንደምትጫወት የልኡካን ቡድኑ አባላት ማንሳታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።
አቶ ደመቀ ከአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት ጋር ለመወያየት አዲስ አበባ ለተገኘው የልዑካን ቡድን ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፥ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል።
#Ethiopia #AU #UN
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!