አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጣልያን ተቋርጦ የነበረውን የአውሮፕላን በረራ ዳግም ልታስጀምር ነው።
የሃገሪቱ መንግስት በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ተቋርጦ የቆየው በረራ ዳግም እንዲጀመር የሚያስችል ስምምነትን ፈርሟል።
የአሁኑ ውሳኔ ከሁለት ወር በላይ ተዘግቶ የቆየውን ሁለገብ እንቅስቃሴ ዳግም ለማስጀመር የተወሰደ ትልቁ እርምጃ ነው ተብሏል።
አሁን በተፈረመው ስምምነት መሰረት ከዓለም አቀፍ በረራዎች በተጨማሪ ከግዛት ግዛት የሚደረጉ በረራዎች የሚጀመሩ ይሆናል።
ከዚህ ባለፈም በቀጣዩ ሳምንት የወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብሮች፣ ምግብ ቤቶችና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ተቋማት ደንበኞቻቸውን ያስተናግዳሉ ተብሏል።
እንዲሁም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንም ለአማኞች ክፍት ይሆናል ነው የተባለው።
ጣልያን በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ክፉኛ የተጎዳች ሲሆን ከ31 ሺህ በላይ ሰዎችም በሃገሪቱ ለህልፈት ተዳርገዋል።
ይሁን እንጅ ከሰሞኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ይነገራል።
ይህን ተከትሎም አንዳንድ ፋብሪካዎችና የህዝብ መዝናኛዎች በተወሰነ መልኩ ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።