አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 6ኛ ዙር 3ኛ አመት የስራ ዘመን የመክፈቻ ስነ-ስርአት የፊታችን ሰኞ ይካሄዳል ።
የምክር ቤቱ የህዝብ ግንኝነት ዳይሬክተር አቶ ያቆብ ወልደሰማያት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም በሚካሄደው የመክፈቻ ስነ- ስርዓት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የምክር ቤቶቹን መከፈት ያበስራሉ።
ከሰዓት በኋላ በሚካሄደው በዚህ የመክፈቻ ስነ- ስርዓት ፕሬዚዳንቷ የመንግስትን የበጀት አመቱን የትኩረት አቅጣጫዎች የሚያመላክት ንግግር ለምክር ቤቱ ያደርጋሉ።
በመክፍቻ ስነ-ስርዓቱ ከምክር ቤቱ አባላት በተጨማሪ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በበላይ ተስፋዬ