የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ ከድር ጁሀር ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Tamrat Bishaw

October 06, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር የሰላም፣ የፍቅር፣ የእርቅ፣የወንድማማችነት፣ የእህትማማችነትና የአንድነት ማሳያ ለሆነው የኢሬቻ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

የተለያዩ የባህል ክንውን የሚከናወንበት የእሬቻ በአል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።

በአሉ የሰላም የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ እና አንዱ አንዱን የሚያግዝበትና ሌሎች ተሞክሮዋችን የምንካፈልበት ከመሆኑም በተጨማሪ አብሮነትንና መተባበርን የሚያጎለብት ታላቅ በዓል ነው ሲሉ መግለፃቸውን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡