የሀገር ውስጥ ዜና

አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ከአሜሪካ ሴናተር ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

October 07, 2023

 

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 26 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ከአሜሪካ ሴናተር ማይክ ሮንድስን ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱም÷ ስለ ሁለቱ ሀገራት ግንኙነትና በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎች ላይ መክረዋል።

በቀጣይም ሁለቱ ሀገራትን ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡