የሀገር ውስጥ ዜና

የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ውይይት እያደረገ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

October 09, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌደሬሽን ምክር ቤት የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እየመከረ ነው፡፡

ኮሚቴው ነገ ከሚካሄደው የፌዴሬሽን ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ጋር ተያያዥነት ባላቸው አጀንዳዎች ላይ ነው እየተወያየ የሚገኘው፡፡

በዚሁ መሠረት በውይይቱ ላይ የኮሚቴው ፀሐፊ ፍቅሬ አማን የ2016 በጀት ዓመት የቋሚ ኮሚቴውን ዕቅድ አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም የተለያዩ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ጉዳዮችን በበጀት ዓመቱ ለመስራት ኮሚቴው እየመከረ መሆኑን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ብሄረሰቦችን አስመልክቶ በተዘጋጀው የጥናት ሰነድ ላይ ከተወያየ በኋላ ሰነዱን ለምክር ቤት ይዞ ይቀርባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!