ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ካነሷቸው ነጥቦች÷
👉 በቀጣይ ሶስት አመታት ሁለንተናዊ የሀገራችንን እድገት ማስቀጠል ዋነኛ አለማችን ነው፣
👉 ልማት እና ጥፋት መሳ ለመሳ ይዞ መጓዝ ለዘላቂ ሀገራዊ እድገት እንቅፋት ነው፣
👉 እንቅፋቶችን ማንሳት፣ የሀገራችንን ዘላቂ እድገት ማፋጠን ለአፍታም የምናቆመው ጉዳይ አይሆንም፣
👉 የህግ የበላይነትን ማረጋገጥና የሰላም መንገዶችን አሟጦ መጠቀም እንዲሁም ዘላቂ ሀገራዊ ሰላምን ለማረጋገጥ መስራት የዚህ አመት የመንግስት ዋና ተግባር ይሆናል፣
👉 የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር የመጀመሪያው መፍትሔ ምርትና ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ማስፋፋት ነው፣
👉 በተናጠልም ይሁን በጋራ በሰላማዊ መንገድ ከማንኛውም ወገን ጋር ለመነጋገር መንግስት ሁልጊዜም ዝግጁ ነው፣
👉 የጎደለውን እየሞላን ያነሰውን እየጨመርን ያልተስማማንበትን እያቆየን በተስማማንበት ላይ እየሰራን በመሄድ ለመጪው ትውልድ የተሻለ ሀገር ማስረከብ ይኖርብናል፣
👉 ለሀገራችን መጻኢ ዘመን በጋራ እንትጋ፣ ከትናንት ይልቅ ጉልበታችንና ጊዜያችንን በነገ ላይ እናውል፣
👉 መነጋገር፣ መከራከርና መግባባት የዚህ ትውልድ መለያ ሊሆን ይገባል፣
👉 ሀገራዊ ገዢ ትርክታችን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ከሁሉም ኢትዮጵያውያን በሁሉም ኢትዮጵያውያን ንቁ ተሳትፎ እውን እንዲሆን ይደረጋል፣
👉 ባለፈው አመት ጅምር ውጤት ያየንበት የጸረ ሌብነት ትግል በዚህ አመትም በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል፣
👉 ህዝቡ በመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚገጥመውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፣
👉 ባለፉት ሶስት አመታት ያስመዘገብነው ጥቅል ሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት በዚህ አመትም 7 ነጥብ 9 በመቶ እንዲሆን በሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች በልዩ ትኩረት ይሰራል፣
👉 በግብርናው ዘርፍ በዚህ አመት ከ22 ነጥብ 1 ሚሊየን ሄክታር መሬት በላይ ይታረሳል፤ ከዚህም 810 ሚሊየን ኩንታል አጠቃላይ የሰብል ምርት ለማሰባሰብ የሚሰራ ይሆናል፣
👉 የመንግስት ገቢ አሰባሰብን ለማሳደግ በዚህ አመት ከታክስ ገቢ 441 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዷል፡፡