አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያና ብሪክስ አባል ሀገራት መካከል ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
በሕንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ከብሪክስ ንግድና እና ኢንዱስትሪ ም/ቤት መስራች ማዱካር (ዶ/ር) እና ምክትል መስራች ሱሺ ሲንግ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷በኢትዮጵያና በብሪክስ አባል ሀገራት መካከል ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያና በብሪክስ መካከል የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትስስርን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡