አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት የተሸጠ ነጠላ ትኬት በታሪክ ሁለተኛው ትልቁ ሎተሪ የሆነውን 1 ነጥብ 76 ቢሊየን ዶላር ማሸነፉ ተሰምቷል።
ፓወርቦል የተባለ የሎተሪ አጫዋች ድርጅት፤ ይህ ክስተት ከመቶ አንድ ሣይሆን ከ292 ነጥብ 2 ሚሊየን አንድ ነው ሲል የአጋጣሚው የመከሰት ዕድል እጅግ የማይጠበቅ መሆኑን ያመለከተው።
ሆኖም የሎተሪ ዕድለኛው ማንነት ይፋ እንዳልሆነም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ከአሁን ቀደም በፈረንጆቹ 2022 ከ2 ቢሊየን በላይ የሎተሪ እጣ የደረሰ ሲሆን፥ ትኬቱ በተመሳሳይ በካሊፎርኒያ ግዛት የወጣ ነበርም ተብሏል፡፡
ትኬቶች እያንዳንዳቸው 2 ዶላር ሲሆኑ፥ በአሜሪካ፣ በፖርቶ ሪኮ እና በአሜሪካ ቨርጂን ደሴቶች ላይ ተሽጠዋልም ነው የተባለው፡፡
የቲኬት ዋጋ እየጨመረ በመምጣቱ ቢሊየን ዶላሮች የሎተሪ ሽልማቶች እየተለመዱ እንደሆኑም ተነስቷል።