የሀገር ውስጥ ዜና

የትምህርት ጥራት ችግሮችን ለመቅረፍ የመምህራን ጉዳይ ሊጤን ይገባል – ምሁራን

By Meseret Awoke

October 14, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተማሪዎች ውጤት ላይ የተመዘገበውን ዝቅተኛ ውጤት ለማሻሻልና የትምህርት ጥራት ችግሮችን ለመቅረፍ የመምህራን ጉዳይ ሊጤን እንደሚገባው ምሁራን ተናገሩ።

ምሁራኑ ለተማሪዎች ውጤት ማሽቆልቆል ሁሉም ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የሥነ-ትምህርት ተመራማሪው  ወርቁ ደጀኔ (ዶ/ር) በትምህርት ዘርፉ ከተስተዋሉ ችግሮች መካከል የመምህራን ምልመላና መረጣ ችግር እንደሚገኝበት አስረድተዋል።

መምህርነት አማራጭ ያጡ ሰዎች የሚቀላቀሉት ሙያ ሆኗል ያሉት ምሁሩ ፥ ይህም የአቅምና የጥራት ችግር እንዲከሰት አድርጓል ነው ያሉት።

የመምህራን የኑሮ ደረጃ ዝቅተኛ መሆን፣ በመምህርነት ሙያ ላይ የሚንጸባረቀው የአመለካከት ዝንፈትና የብቃት ማነስ በዘርፉ ለገጠሙ ችግሮች መነሾ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ ተስፋ ተገኘ (ዶ/ር) ናቸው።

እነዚህን ችግሮች ለማረምም መንግስትን ጨምሮ ስለትውልድና ሀገር ያገባኛል የሚል ሁሉ ሊረባረብ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

በአፈወርቅ እያዩ