አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2020 የስነ-ጽሁፍ ዘርፍ ኖቤል አሸናፊዋ አሜሪካዊት ገጣሚ ሉዊስ ግለክ በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የተለያዩ ዘገባዎች ገለጹ።
በያል ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ፕሮፌሰር የነበሩት ግለክ የመጀመሪያ የግጥም ሥራ ስብስባቸውን በፈረንጆቹ 1968 ‘ፈርስትቦርን’ በሚል ርዕስ ማሳተማቸው ተገልጿል።
በግጥምና በወግ ጸሐፊነታቸው ይታወቁ የነበሩት ግለክ ‘ዘ ዋይልድ አይሪስ’ በሚለው ሥራቸው በፈረንጆቹ 1993 የፑልቲዘርን አሸንፈዋል።
በፈረንጆቹ 2003/4 የአሜሪካ የስነ-ግጥም ሎሬት ሆነው ያገለገሉት ግለክ፤ በፈረንጆቹ 2016 ከቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ብሔራዊ ሜዳሊያ ሽልማት ተቀብለዋል።
ግለክ በህይወት ዘመናቸው 12 የግጥም ስብስቦችን የያዘ 12 መድብል ያሳተሙ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያለው ወግ ጽፈው ለንባብ ያበቁ ነበሩ።