የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ “በኤየር ካርጎ ኒውስ አዋርድ 2023” በሁለት ዘርፍ አሸነፈ

By Shambel Mihret

October 14, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነትና ሎጂስቲክስ  ዘርፍ “በኤየር ካርጎ ኒውስ አዋርድ 2023” በሁለት ዘርፎች አሸንፏል፡፡

አየር መንገዱ የዓመቱ ምርጥ የጭነት አየርመንገድ ሽልማትን ለ2ኛ ጊዜ እንዲሁም የአፍሪካ ምርጥ የጭነት አየር መንገድ ሽልማትን ለተከታታይ 5 ዓመታት በማሸነፍ ነው የተሸለመው፡፡

ሽልማቱን ተከትሎ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው÷ “በኤየር ካርጎ ኒውስ አዋርድ 2023” በ2 ዘርፍ ሽልማት በመቀዳጀታችን ከፍ ያለ ኩራት ተሰምቶናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለደንበኞች ቀልጣፋ እና አስተማማኝ አገልግሎት መስጠቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡