የሀገር ውስጥ ዜና

አርቲስት ሐሎ ዳዌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

By Shambel Mihret

October 14, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት ሐሎ ዳዌ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡

በኦሮሞ የኪነ-ጥበብ እድገት ውስጥ አስተዋጽኦ ካበረከቱ ታዋቂ አርቲስቶች አንዷ የሆነችው አርቲስት ሐሎ ዳዌ ባደረባት ሕመም ለረጅም ጊዜ ሕክምና ስትከታተል መቆየቷ ተመላክቷል፡፡

ይሁን እንጂ ከሕመሟ ማገገም ሳትችል ቀርታ በዛሬው ዕለት አዳማ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ተገልጿል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለአርቲስት ሐሎ ዳዌ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ የሙያ አጋሮች እና አድናቂዎች መጽናናትን ይመኛል፡፡