የሀገር ውስጥ ዜና

በተለያዩ ማዕከላት የሚገኙ ሠልጣኞች የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

By Feven Bishaw

October 15, 2023

 

በአዲስ አበባ ማዕከል ስልጠናቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ አመራሮች የከተማዋን ግዙፍና ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች በዘጋቢ ፊልም የተመለከቱ ሲሆን አንዳንዶችንም በአካል በመጎብኘት ልምድ እንዲቀስሙ እየተደረገ ነው።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ስልጠናው ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት መንግስትን ለማጠናከር በጊዜ ቀመር የተቀመጡ የፓርቲያችንን ራዕይዎች ለማሳካት እርስ በእርስ መማማርን ዓላማው አድርጎ እየተካሄደ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በተመሳሳይ በአርባ ምንጭ ማዕከል ያሉ ሰልጣኞች÷ በጋሞ ልማት ማህበር የአርባምንጭ ግብርና ልማት እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል፡፡

እንዲሁም የጅግጅጋ የስልጠና ማዕከል ስልጠኞች በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን በሸበሌ የሚገኝ ዘመናዊ የግመል እርባታ ካምፕን ፣ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የሚገኘው ዶሮ እርባታ ፣ የቱሉ ጉሌድ እርሻ ፣ የፋፈን የእርሻ ማሳ እና የተሰሩ የውሃ መሠረተ ልማት ጎብኝተዋል፡፡