አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መላው ኢትዮጵያውያን ለሰንደቅ ዓላማ ከፍታና ክብር ዘብ መቆም አለባቸው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለጹ፡፡
16ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየተከበረ ይገኛል፡፡
በመርሐ ግብሩ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ተገኝተዋል፡፡
በተጨማሪም የሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት፣ የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር አባላት እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
ቀኑ “የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አድርሰዋል፡፡
አፈ ጉባኤው “ሰንደቅ ዓላማችን የነጻነታችን፣ የአንድነታችን፣ የጀግንነታችን፣ የአርበኝነታችን፣ የሉዓላዊነታችን እና የኢትዮጵያዊነታችን ዓርማ ነው ብለዋል፡፡
አክለውም ሰንደቅ ዓላማችን ከትውልድ ትውልድ የተሻገረ የመስዕዋትነትና የሀገር አደራ ምልክት እንደሆነ ጠቅሰው፥ መላው ኢትዮጵያውያን ለሰንደቅ ዓላማ ከፍታና ክብር ዘብ መቆም አለባቸው ሲሉም ነው የገለጹት፡፡
በመሰረት አወቀ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!