አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 16ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተከብሯል፡፡
ቀኑ “የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተከበረው፡፡
በኦሮሚያ ክልል በሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች የመንግስት ስራ ሃላፊዎች እና ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል፡፡
የጨፌ ኦሮሚያ አፈጉባዔ ሰዓዳ አብዱረህማን ሰንደቅ ዓላማ የሀገር ክብርና መገለጫ መሆኑን አንስተው፥ ቀደምት አባቶች ኢትዮጵያን ለማፅናት ለሰንደቅ ዓላማ ክብር ሲሉ ትልቅ መስዋዕትነት መክፈላቸውን አስታውሰዋል።
በተመሳሳይ በሲዳማ ክልል፣ በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 16ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ ሁነቶች የመንግስት ሰራተኞ እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ተከብሯል፡፡
በወንድሙ አዱኛ እና ጥላሁን ይልማ
#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!