የሀገር ውስጥ ዜና

16ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተከበረ

By Melaku Gedif

October 16, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 16ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተከብሯል፡፡

በመርሐ ግብሩ ፥ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም የሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት፣ የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር አባላት እና ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

ቀኑ “የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተከበረው፡፡

በፍቅርተ ከበደ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!