የሀገር ውስጥ ዜና

በትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By ዮሐንስ ደርበው

October 16, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ዳሌ ሰዲ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስምንት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

የወረዳው ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት የትራፊክ ደኅንነት ተቆጣጣሪ አረጋ መንገሻ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ዛሬ ጠዋት 2፡00 ገደማ በደረሰው የትራፊክ አደጋ በአራት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

አደጋው የተከሰተው÷ በተለምዶ ‘ዶልፊን’ እየተባለ የሚጠራው መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ‘ኤፍ ኤስ አር’ ተብሎ ከሚጠራው የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨታቸው ነው ብለዋል፡፡

በገላና ተስፋ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!