የሀገር ውስጥ ዜና

የነጭ ሽንኩርት የጤና በረከቶች

By Meseret Awoke

October 18, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ የተካሄዱ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ነጭ ሽንኩርት ከፍተኛ የመድሐኒት ባህሪ ያላቸው ውህዶችን የያዘ ሲሆን፥ ይህም የጤና ጠቀሜታውን ከፍ ያደርገዋል፡፡

በብዙ የዓለም ክፍሎች የሚገኘው ነጭ ሽንኩርት፥ በጠንካራ ጠረኑና በጣዕሙ ምክንያት በምግብ ዝግጅት ውስጥ ተወዳጅ ንጥረ ነገር ነው።

በነጭ ሽንኩርት ውስጥ የሰልፈር ውህዶች ስለሚገኙ ወደ ሰውነትዎ በመግባት ጠቃሚ የጤና በረከቶችን ይሰጥዎታል፡፡

ነጭ ሽንኩርት ገንቢ ተክል ቢሆንም በተጨማሪም በጣም ጥቂት ካሎሪዎች እንዳሉት ይነገራል፡፡ ይህም ማንጋኒዝ፣ ቫይታሚን ቢ6፣ ቫይታሚን ሲ፣ ሴሊኒየም እና ፋይበር ይገኙበታል፡፡

ነጭ ሽንኩርት ጉንፋንን ጨምሮ የተለያዩ ቅዝቃዜ የሚያመጣቸውን በሽታዎችን ለመከላከል ይረዳል፡፡

በነጭ ሽንኩርት ውስጥ ያሉ ውህዶች የደም ግፊት እንዲቀንስ ይረዳሉ።

ነጭ ሽንኩርት የኮሌስትሮል መጠንን የሚያሻሽል ሲሆን፥ ይህም ለልብ ሕመም የመጋለጥ እድልን እንደሚቀንስ ይነገራል፡፡

ሆኖም በአጠቃቀምዎ (በመጠን ልኬትዎ) ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

ነጭ ሽንኩርት የሕዋስ ጉዳት እና እርጅናን ለመከላከል የሚረዱ ፀረ-ኦክሳይዶችን ይዟል። ይህም የአልዛይመር በሽታን እና ሌሎች የመርሳት ዓይነት በሽታዎች ተጋላጭነትን ሊቀንስ ይችላል።

ሥር የሰደዱ በሽታዎችን ለማከም የሚረዳው ነጭ ሽንኩርት፥ ይህም ረጅም እድሜ ለመኖር የሚረዳ እንደሆነ ኽልዝላይን በመረጃው አንስቷል፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ነጭ ሽንኩርት መመረዝ እና ተያያዥ በሽታዎችን በእጅጉ እንደሚቀንስም ይነገራል።

በተጨማሪም ነጭ ሽንኩርት የአጥንት ጤና የሚያሻሽል ነው።

ሆኖም ግን ነጭ ሽንኩርት የጎንዮሽ ጉዳቶች አሉት፥ እነዚህም እንደ መጥፎ የአፍ ጠረን እንዲሁም አለርጂ ይጠቀሳሉ፡፡

በተጨማሪም የደም መፍሰስ ችግር ካለብዎ ወይም የደም መርጋት ለመከላከል የሚያስችሉ መድኃኒቶችን እየወሰዱ ከሆነ ነጭ ሽንኩርት ከመውሰድዎ በፊት ሃኪምዎን ያማክሩ፡፡