የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በ3ኛው የቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም ላይ ንግግር አደረጉ

By ዮሐንስ ደርበው

October 18, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ3ኛው የቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም መክፈቻ መርሐ- ግብር ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡

በንግግራቸውም÷ የቻይና-አፍሪካን ግንኙነት ጥንተ መሰረት እና እድገት አውስተዋል፡፡

በቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም የመሰረተ ልማት ክንውን በአፍሪካ አህጉር የተጣለውን ጠንካራ የትብብር መሰረትም  አንስተዋል::

በማደግ ላይ ያለውን የአፍሪካን ተፅእኖ የመፍጠር አቅም አፅንዖት የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ በባለብዙ ወገን መድረኮች አካታችነትን ማረጋገጥ ተገቢ መሆኑን አስረድተዋል::