የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ ከድር ጁሀር የደቻቱ ወንዝ ፕሮጀክትን ለማስጀመር ከተለያዩ ሀገራት ከተውጣጣ ልዑክ ጋር ተወያዩ

By Shambel Mihret

October 18, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር የደቻቱ ወንዝ ፕሮጀክትን ለማስጀመር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ ስምንት የዓለም ሀገራት ተውጣጥተው ከመጡ ልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዛሬው ዕለት በደቻቱ ወንዝ ፕሮጀክት ጅማሮና ፋይዳ ላይ ልዑካን ቡድኑ፣ ከንቲባ ከድር ጁሀር እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የውይይት መድረክተካሂዷል፡፡

በዚህ ወቅት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር÷ፕሮጀክቱ ለድሬዳዋ መስተዳደር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

ለፕሮጀክቱ መሳካትም መስተዳደሩ ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ከንቲባው ጠቅሰዋል፡፡

የደብሊው አር አይ ዳይሬክተር አክሊሉ ፍቅረ ስላሴ (ዶ/ር)÷ስለፕሮጀክቱ ገለጻ ማድረጋቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በመድረኩ በድሬዳዋ አካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን የአካባቢ ሕግ ተከባሪነትና የአካባቢና ማህበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ ቡድን መሪ አቶ ደረጀ አቢቲ÷ በአፈርና ውሃ ጥበቃ፣ በአረንጓዴ አሻራ የተሰሩ ስራዎች ሰነድ ቀርቦ ከልዑካን ቡድኑ ጋር ውይይት ተደርጓል።