አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ ጋር ተወያይተዋል።
ሚኒስትር ዴዔታው ለአምባሳደሩ የእንኳን ደህና መጡ መልዕክታቸውን ካስተላለፉ በኋላ፥ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን መድረኮች ላይ የሚያደርጉትን ትብብር አድንቀዋል።
የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር እና የተቀናጀ ውይይትን ማደስ ያለውን አስተዋጽዖም አመላክተዋል።
አምባሳደር ምስጋኑ አክለውም፥ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላትን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እና የንግድ ግንኙነት ለማሳደግ ያላት ፍላጎትም ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
አምባሳደር ማሲንጋ በበኩላቸው፥ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነቷ ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነትና ፍላጎት ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#Ethiopia #USA
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!