የሀገር ውስጥ ዜና

በአሶሳ ከተማ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 4 ነጥብ 9 ኪሎ ግራም ወርቅ ተያዘ

By Melaku Gedif

October 20, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሶሳ ከተማ አስተዳደር በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 4 ነጥብ 9 ኪሎ ግራም ወርቅ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ሕገ-ወጥ ወርቁ የተየያዘው በአሶሳ ከተማ አዲስ አበባ መውጫ ኬላ ላይ የክልሉ የአድማ ብተና ልዩ ጥበቃ ፖሊስ አመራሮች እና አባላት ከፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር ባደረጉት ክትትል መሆኑ ተገልጿል፡፡

አዘዋዋሪዎቹ በተለያየ ተሽከርካሪ በመሳፈር ወርቁን በጫማቸው ውስጥ በመደበቅ የፍተሻ ኬላውን ለማለፍ ሲሞክሩ በተደረገው ፍተሻ መያዛቸውን የክልሉ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

በፖሊስ ማስረጃነት ከእነተጠርጣሪዎቹ የተያዘው ወርቅ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝም ተጠቅሷል፡፡