የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀድያ ሆሳዕና እና ወልቂጤ ከነማ ነጥብ ተጋሩ

By Feven Bishaw

October 20, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ3ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀድያ ሆሳዕና እና ወልቂጤ ከነማ አቻ ተለያይተዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

ውጤቱን ተክትሎ በፕሪሚየር ሊጉ ደካማ ጅማሮ ካሳዩት ክለቦች አንዱ የሆነው ሀድያ ሆሳዕና በሶስት ጨዋታዎች 1 ነጥብ ብቻ በመሰብሰብ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

በተመሳሳይ ወልቂጤ ከተማ በሶስት ጨዋታዎች ሁለት ነጥብ በመያዝ በሊጉ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

የ3ኛ ሳምንት መርሃ ግብሮች መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ ምሽት 12 ሰዓት ላይ መሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሻሸመኔ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡