አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የወጣቶች ስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራን በዛሬው ዕለት መርቀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ “ሁሉም በየመስኩ አድርጎ በማሳየት፣ ሆኖ በመገኘት እና በጎ አርዓያ በመሆን ኃላፊነቱን ቢወጣ ኢትዮጵያ የወጣቶች ሀገር በመሆኗ ዛሬ የዘራነው መልካም ዘር ነገ መልካም ውጤት ያመጣል” ብለዋል።
ዛሬ የተመረቀው የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራ ለሕፃናት እና ለወጣቶች አገልግሎት የሚውል መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡