የሀገር ውስጥ ዜና

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከደቡብ አፍሪካው ኢታማዦር ሹም ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

October 24, 2023

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 13 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከደቡብ አፍሪካው ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሩድዛኒን ማፕዋንያ ጋር ተወያይተዋል።

የደቡብ አፍሪካው ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሩድዛኒን ማፕዋንያ በኢትዮጵያ እና በደቡብ አፍሪካ ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት እና ትብብር ለማጠናከር ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር ተነጋግረዋል።

ኢታማዦር ሹሙ 116ኛውን የሠራዊት ቀን በክብር ለመታደም አዲስ አበባ ከባለቤታቸው ጋር መግባታቸውን የመከላከያ ሰራዊት ገጽ መረጃ ያመላክታል።