አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ጄ. ማሲንጋን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይታቸውም÷ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በይበልጥ ለማጠናከር ለሚከናወኑ ሥራዎችም አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ እንደሚደረግ አቶ ደመቀ አረጋግጠዋል፡፡
አምባሳደር ማሲንጋ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላት የኢኮኖሚ ትብብር ዐቅሟን ለማውጣትና ለማሣደግ እንደሚያግዛት አመላክተዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!