የሀገር ውስጥ ዜና

በሸገር ከተማ የተሠሩ የልማት ሥራዎች ተጎበኙ

By ዮሐንስ ደርበው

October 25, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሸገር ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተሠሩ የልማት ሥራዎች ተጎብኝተዋል፡፡

ከተጎበኙት የልማት ሥራዎች መካከል በመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ተደራጅተው በዶሮ እርባታ፣ በከብት ማደለብ እና በወተት ላም ላይ እያከናወኑት ያለው ሥራ ይገኝበታል፡፡

የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) በጉብኝቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ “በከተማዋ የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሠራን እንገኛለን” ብለዋል።

የከተማዋ ምስረታ ጠንካራ ኢኮኖሚ መፍጠር እና ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ በመሆኑ አሁን እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎች የሚደነቁ ናቸው ነው ያሉት፡፡

ጉብኝቱ በገላንና ሌሎች ክፍለ ከተሞች እንደሚቀጥልም ተመላክቷል፡፡

በአዳነች አበበ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!