አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልሉን የተፈጥሮ ጸጋና ሃብትን በማልማት በክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ እንደሚሠራ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው ገለጹ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥረታ ማጠቃለያ መርሐ- ግብር በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል፡፡
አቶ እንደሻው ጣሰው በመርሐ- ግብሩ እንደተናገሩት÷ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘርፈ ብዙ አቅም ያለው መሆኑን አንስተዋል፡፡
የክልሉ ሕዝቦች በአዲስ ምዕራፍ፣ በአዲስ ተስፋ፣ በጋራ እንደሚሠሩ ገልጸው÷ ሕዝቡ ሙሉ አቅሙን ለሰላም ግንባታና ልማት እንዲያውል ጠይቀዋል።
በበረከት ተካልኝ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!